የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ዓላማ‌ የናሙና ክፍሎች

የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ዓላማ‌. ማንኛውም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የሚከተሉትን ዓላማዎች ለማሳካት የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ በማዘጋጀት በጠ/ጉባኤ አስፀድቆ ተግባራዊ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ • የማህበሩ አስተዳደር አና የገንዘብ አመራር ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ በውጤታማና ቀልጣፋ በሆነ መልኩ ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ፣ • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአገልግሎት ክልል ውስጥ ያለው የመስኖ አውታር አሰራርና ጥገና በተገቢው ሁኔታ ለመከታተልና የመስኖ ውሃ ክፍፍል በቅልጥፍናና ፍትሀዊ በሆነ አግባብ መፈፀሙን ለመረጋገጥ፣ • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአገልግሎት ክልል ውስጥ በማኅበሩ አመራር እና በመስኖ አውታሩ አሰራርና ጥገና በከፍተኛ ደረጃ ግልጽነትና ተጠያቂነት በማስፈን በማኅበሩ ሊከሰቱ የሚችሉ ውስጣዊ ግጭቶችን ለማስወገድ፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበርን ለማቋቋምና ለማስተዳደር የወጣውን የፌደራል አዋጅ ቁጥር 841/2014 እና የክልሉን አዋጅ ቁጥር 239/2008፣ የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም የማኅበሩን የውስጥ ደንብ በሚጥሱ ተጠቃሚዎች አስፈላጊውን አስተዳደራዊ የቅጣት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አሰራር ለመዘርጋትና በሁሉም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ሰርዓት መስፈኑን ለማረጋገጥ፣ ? የስልጠናውን ተሳታፊዎች በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ከማኅበሩ አመራር እና ከመስኖ አውታሩ አሰራርና ጥገና ጋር በተያያዘ ምን ምን ጉዳዮች መካተት አለባቸው የሚል ጥያቄ በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊዎች ሀሳብ እንዲሰጡበት አድርግ፡፡ የሚሰጡትን መልስ በፊሊፕ ቻርት ወይም በነጭ ሰሌዳ ጻፍ፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ ድንጋጌ ቢያንስ ከሚከተሉት ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ነጥቦችን ማካተት አለበት፡፡ • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአባልነት መቀበያ መስፈርት፣ • የአባላት የመመዝገቢያ ክፍያ፣ • ለማኅበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ፣ ለቁጥጥር ኮሚቴ፣ ለግጭት አስታራቂና አስወጋጅ ኮሚቴ በማኅበሩ ስራ ምክንያት ላወጡት ወጪ ማካካሻ አከፋፈል ስርዓትና የሚከፈለውን መጠን፣ • የጠቅላላ ጉባኤ አመታዊ ሰብስባ እና የስራ አመራር ኮሚቴ ስብስባ ሰርዓትና የሰብሰባ ጊዜ፣ • የጠቅላላ ጉባኤና የስራ አመራር ኮሚቴ የድምጽ አሰጣጥ ስርዓትና ምልዓተ ጉባኤ፣ • በጠቅላላ ጉባኤ እና/ወይም በስራ አመራር ኮሚቴ የተመረጡ ንዑሳን ኮሚቴዎች ተግባርና ኃላፊነት፣ • አመታዊ የመስኖ አውታር ጥገና እና ቁጥጥር የሚካሄድበትን ስርዓትና ጊዜውን፣ • ዓመታዊ የስራ ዕቅድ እና ዓመታዊ ሪፖርት የሚዘጋጅበትንና የሚጸድቅበትን ስርዓትና ጊዜ፣ • በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስለሚቀጠሩ ቅጥር ሰራተኞች የቅጥር፣ የስንብት እና ዋና ዋና ተግባርና ኃለፊነታቸው ዝርዝር፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አባላት የውሃ አገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉበትን ሰርዓትና ጊዜውን፣ • የመሰኖ ወሃ አገልግሎት ክፍያ ባልከፈሉ ተጠቃሚዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ማኅበሩ ስላለው ስልጣን፣ በወቅቱ ባልከፈሉ ተጠቃሚዎች የሚወሰድ አስተዳደረዊ የቅጣት እርምጃ አወሳሰድ ስርዓትና የመክፈያ ጊዜውን ጭምር፣ • የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበሩ ከሌላ አንድ ማኅበር ወይም ከአንድ በላይ ከሆኑ ማኅበራት ጋር ስለሚዋሃድበት፣ የፌዴሬሽን አባል ስለሚሆንበት ስርዓት፣ • የማኅበሩን እና የአባላትን የኃላፊነት ደረጃ፣ • ማኅበሩ በሚፈርስበት ጊዜ የማፍረስ ሂደቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ሀብት የሚከፋፈልበትን ስርዓት፣ • የውስጥና የውጭ ግጭቶች ስለሚፈቱበት ስርዓት የመሳሰሉት ነጥቦች ሊከተቱ ይገባል፡፡ 2.4.2.1 የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ የሚፀድቅበትና የሚሻሻልበት ስርዓት‌ የውስጥ መተዳደሪያ ረቂቅ በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ወቅት ቀርቦ በጉባኤው አብላጫ ድምጽ መጽደቅ አለበት፡፡ የፀደቀው የውስጥ መተዳደሪያ ደንብ በማንኛውም ጊዜ በጠቅላላ ጉባኤ አብላጫ ድምጽ ሊሻሻል ይችላል፡፡ የውስጥ መተዳደሪያ ደንቡ ወይም ሌላ የማሻሻያ ጥያቄ ሲኖር የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ በተካሄደ በ15 ቀናት ውስጥ ለተቆጣጣሪው አካል መቅረብ አለበት፣ 2.4.3 ውጤታማ ቅጣት /Effective sanctions/‌ ? የስልጠናውን ተሳታፊዎች በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት ምን የቅጣት አይነቶች ሊጠቀሙ ይገባቸዋል? የትኞቹ ናቸው የበለጠ ውጤታማ ሊሆኑ የሚችሉት የሚሉ ጥያቄዎችን በመጠየቅ ሁሉም ተሳታፊዎች ሃሳብ እንዲሰጡበት በማድረግ የሚሰጡትን መልስ በፊሊፕ ቻርት ወይም በነጭ ሰሌዳ ጻፍ፡፡ አንድ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የማኅበሩን መተዳደሪያ ደንብ እና የውስጥ መተዳደሪያ...