የጥሩ/መልካም ስራ አመራር መርሆዎች‌ የናሙና ክፍሎች

የጥሩ/መልካም ስራ አመራር መርሆዎች‌. የኃላፊነትና የተጠያቂነት ስሜት፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አመራር አባላት በማኅበሩ አገልግሎት ክልል ውስጥ ላሉ ለሁሉም የመስኖ ተጠቃሚዎች በእኩልነት እያገለገሉ መሆኑንና ተጠሪነታቸውም ለመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች አባላት መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡ • ተግባርን መገንዘብ፣ ምን ተግባር መሰራትና መቸ መሰራት እንዳለበት ማወቅ፣ • እርምጃ የመውሰድ ተነሳሽነት፣ ስራዎችን ለመፈፀም ወይም ችግሮችን ለመፍታት መነሳሳት፣ • የስራ ክፍፍል፣ ሌሎቹ በስራው ተሳታፊ እንዲሆኑ የማነሳሳት፣ የቡድን ስራ የማጠናከር፣ የተጠቃሚውን ክህሎት ለስራ የመጠቀም አቅም፣ • ትክክለኛ ውስኔ መወሰን፣ ማንኛውም ውሳኔ ሲወሰን ትክክለኛና ተቀባይነት ያለው ውሳኔ መወሰን፣ • ውጤታማነት በፍጥነት ውጤት በሚገኝባቸው ተግባራት ማተኮር፣ ወጭን መቆጣጣር • ብልሀት፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችንና አለመግባበቶችን በብልሀት የመፍታት ክህሎት፣ • አደረጃጀት፣ ጥሩ የሆነ አስተዳደራዊ አደረጃጀትና የፋይናነስ አመራር ክህሎት መኖር፣ • ግልፀኝነት፣ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አባላት /እና አባል ያልሆኑ ተጠቃሚዎች/ በአመራር አካላት ውሳኔዎች፣ በተግባራት አፈጻፀም እና የማኅበሩ የገንዘብ አጠቃቀም በወቅቱና ውጤታማ ለሆነ ጉዳይ ስራ ላይ መዋሉን ግልጽ ማድረግ፣ • የግንኙነት ክህሎት፣ ከማኅበሩ አባላት ጋር፣ ከወረዳ አስተዳደር፣ ከቀበሌ አስተዳደርና ከሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር መልካም ግንኙነት እንዲኖር ማድረግ፣ እነዚህ የስራ አመራር መርሆዎች አብዛኘዎቹ በራሳቸው ገላጭ በመሆናቸው በዚህ የስልጠና ማኑዋል ሌላ ዝርዝር ነገር አልተካተተም፡፡ ለማንኛውም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ለጥሩ ስራ አመራር ወሳኝ በመሆናቸው ቀጥሎ ባለው ክፍል ተብራርተዋል፡፡ 3.1.1.2 ግልፀኝነት እና ተጠያቂነት፣‌ በአንድ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ውስጥ ዘላቂነት ያለው አሰራር ለማረጋገጥና ውጤታማ ለመሆን፣ ለተጠቃሚዎች ተጠያቂ መሆን እና ግልጽ ውሳኔዎችን መወሰን ወሳኝና መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ • ተጠያቂነት፡- ተጠያቂነት ማለት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአመራር አባላት ሊቀመንበሩን ጨምሮ የሚሰሩትን ተግባር አፈጻፀም ለማኅበሩ አበላት ግልጽ የማድረግና ባልፈፀሟቸው ተግባራትም ተጠያቂ የመሆን ግዴታ አለባቸው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የአመራር አባላት የሚመረጡት በማኅበሩ አባላት ሲሆን ጠቅላላ አባላትን በመወከል የዕለት ከዕለት ሥራዎችን ያከናውናሉ፡፡ • ግልፀኝነት፡- በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ከተጠያቂነት ተቀራራቢ የሆነው ጉዳይ ግልፀኝነት ያለው የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ነው፡፡ ግልፀኝነት ማለት የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስራ አመራ ኮሚቴ ማንኛውንም የኮሚቴ ውሳኔዎችንና ተግባራትን ለአብነት የገንዘብ አጠቃቀምን ለሁሉም ተጠቃሚዎች ግልጽ ማድረግ ማለት ነው፡፡ ☞ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ውጤታማ ስራ ለመስራት ቅድመ ሁኔታዎች በአባላትና አባል ባልሆኑ ተጠቃሚዎች ዘንድ እምነትንና ተቀባይነትን ለመገንባት ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ መሆንና የኮሚቴውን ባህሪ፣ ተግባራት እና ውሳኔዎችን በሚመለከት በግልጽ ለተጠቃሚዎች ማስገንዘብ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስራ አመራር ኮሚቴ የአባላትንና አባል ያልሆኑ ተጠቃሚዎችን ጥቅም ለማስከበር የሚችሉትን አቅም ተጠቅመው የተሰጣቸወን ተግባር መፈፀምና አፈጻፀሙንም ለአባላት ማሳየት መቻል አለባቸው፡፡ በማኅበሩ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ወቅት የማኅበሩ ሊቀመንበር ዓመታዊ ሪፖርት አጠቃላይ የተግባራቱን አፈጻፀም በሚያሳይና ሌሎችንም ጉዳዮች ባካተተ መልኩ ሌሎችን የአመራር አባላት ወክሎ ተጠያቂነትና ግልጽነት ባለው ሁኔታ ለሁሉም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አባላት ማቅረብ አለበት፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የሚከተሉት ሁለት ዓይነት ተጠያቂነቶች አሉት፣ • ሙያዊ ተጠያቂነት፣ የመስኖ አውታሩን አሰራርና ጥገና በወቅቱ ከማከናወን ጋር የሚገናኝ ሲሆን ለዚህም ማኅበሩ ኃላፊነት አለበት፣ • በገንዘብ ነክ ጉዳዮች ተጠያቂነት፣ ይህ የማኅበሩን የገንዘብ ነክ ጉዳዮች በአግባቡ መምራትን፣ የገንዘብ አጠቃቀም ትክክለኛ ሪፖርት ማቅረብ ጋር የሚያገናኝ ነው፡፡ የሙያዊ እና የገንዘብ ነክ ጉዳዮች ተጠያቂነት እንዲሁም ግልፀኝነት እጥረት መኖር ገንዘብን አላግባብ መጠቀምና ብክነትን ስለሚያስከትል ለአብዛኛዎቹ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበራት መዳከም ዋና ምክንያቶች ናቸው፡፡ የዚህም የመጨረሻ ውጤት የሚሆነው የመስኖና ድሬኔጅ መሰረተ ልማት በወቅቱና ውጤታ...