ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ሰነዶች አያያዝና አጠባበቅ‌ የናሙና ክፍሎች

ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ሰነዶች አያያዝና አጠባበቅ‌. ዓላማ፣ • ሰልጣኞች በአግባቡ የተመሰረተና የተደራጀ የአስተዳደራዊ አሰራር ስርዓት የመኖር ዓለማና ጠቀሜታ ላይ ጥሩ ግንዛቤ ይኖራቸዋል፡፡ • ተሳታፊዎች በጥንቃቄ መያዝ ስላለባቸውና መሰረታዊ መረጃዎችን የያዙ የተለያዩ መዛግብትና ሰነዶች ብዛታቸውን ጨምሮ ዕውቅና ይኖራቸዋል፡፡ • ሁሉም የስልጠናው ተሳታፊ የተላያዩ ገንዘብ ነክ ባልሆኑ ሰነዶች አዘገጃጀት እና አጠባበቅ ይሳተፋሉ፡፡ ርዕሶች፣ • የአስተዳደረዊ አመራር አጠቃላይ መርሆዎች፣ o የአስተዳደረዊ አመራር ዓለማ • የማኅበሩ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ መረጃዎች o የአባላት መዝገብ o የመሬት ይዞታ መዝገብ o ህጋዊ የምዝገባ ሰነድ o የስራ አመራር ኮሚቴ እና የቁጥጥር ኮሚቴ መዝገብ o የሙያ መዝገብ/ thechinical register/ o የጥገና መዝገብ o የመስኖ ውሃ ስርጭት መዝገብ o የንብረት መዝገብ o የመጋዘን መቆጣጠሪያ መዝገብ o ፕሮቶኮል /የደብዳቤ ወጭና ገቢ ማድረጊያ/መዝገብ o የቃለ ጉባኤ መዝገብ o የቅሬታዎች መመዝገቢያ መዝገብ o ኦዲት ሬፖርት • ተሳታፊዎች፣ የማኅበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ አባላት፣ • የስልጠና መሳሪያዎች፡- ፊሊፕ ቻርት እና ማኑዋል፣ • ስልጠናው የሚወስደው ጊዜ፡- 3፡30 /ሶስት ሰዓት ተኩል/፣ 3.3.1 የአስተዳደራዊ አመራር አጠቃላይ መርሆዎች፣‌ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር የሚመሰረተው በግለሰቦች የጋራ ፍለጎት በዋናነትም የመስኖ መሬታቸውን ለማልማት በሚፈልጉ ሰዎች ነው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር በቂ አገልገሎት ለተጠቃሚዎች ለመስጠት በተለይም በማኅበሩ አገልግሎት ክልል ውስጥ በበቂ መጠንና እና ፍትሃዊ የመስኖ ውሃ አቅርቦት እንዲኖር ለማስቻል ተግባራትን የሚያከናውኑ አመራር አባላት ከጠቅላላው አባላት ውስጥ እንዲመረጡ ይደረጋል፡፡ ማኅበሩን በአግባቡ ለመምራት የተመረጡ አመራር አካላት በአብዛኛው አባላት እምነት የተጣለባቸውና ኃላፊነታቸውን ሊወጡ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አመራር አካላት በተጠቃሚዎች በተለይም በአባላት ዘንድ ሙሉ ታማኝነታቸው ሊረጋገጥ የሚችለው ሁሉም የማኅበሩ ጉዳዮች ግልጽና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ ሲፈፀሙና ሁሉም የመስኖ ውሃ ተጠቃሚ ልዩ ልዩ አገልግሎቶችን ለመስጠት በማኅበሩ እየተሰራ ያለውን ስራ ምን እና እንዴት እየተሰራ እንደሆነ ሙሉ በሙሉ ሲገነዘቡ ብቻ ነው፡፡ ? የስልጠናው ተሳታፊዎችን በመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ያሉ ተግባራትን በአግባቡ ለመፈፀም አስተዳደራዊ አመራር መኖር ያለው ጠቀሜታ ምንድን ነው የሚል ጥያቄ በመጠየቅ የሚሰጡትን መልሰ በፊሊፕ ቻርት ወይም በነጭ ሰሌዳ ጻፍ፡፡ በመስኖ ውሃ ተጠቃሚወች ማኅበር የፋይናንስ እና አስተዳደራዊ አመራር ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ መፈፀሙን ለማረጋገጥ ሁሉንም ተግባራት መዝግቦ መያዝ ወሳኝ ጉዳይ ነው፡፡ ይህም ሊያስገኝ የሚችለው ጠቀሜታ፡- • የስራ አመራር ኮሚቴው የመስኖ አውታሩን የዕለት ከዕለት ስራዎችን ለመቆጣጠርና ችግሮች ካሉ ወይም በሚፈጠሩበት ጊዜ እርምጃ ለመውሰድ፣ • የማኅበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ ለቁጥጥር ኮሚቴው እና ለጠቅላላ ጉባኤው በመስኖ አሰራርና ጥገና ዙሪያ ያለውን የማኅበሩን አፈፃፀም በትክክል መረጃ መሰጠት ያስችላል፣ • የማኅበር አባላት በማንኛውም ጊዜ የማህበሩን መዛግብቶችና ሰነዶች ማየት ይችላሉ፣ • የቁጥጥር ኮሚቴው በመስኖ አውታሩ አሰራርና ጥገናን በሚመለከት የቁጥጥርና ኦዲት ስራ በመስራት የስራ አመራር ኮሚቴውን የተግባራት አፈፃፀም እንዲሁም የማኅበሩን አፈፃፀም ለማጥናት፣ 3.3.2