መግቢያ የናሙና ክፍሎች
መግቢያ. በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት እና በቱርክ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል እ.ኤ.አ. ሜይ 10 ቀን 2022 በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብር ስምምነት በአንካራ (ቱርክ) ተፈርሟል። በስምምነቱ መግቢያ ላይ ስምምነቱ በወንጀል ምርመራ፣ ክስ እና የክርክር ሂደት የሁለቱንም ሀገራት የህግ አካላት ዉጤታማ በማድረግ የወንጀል መከላከል ስራን ዉጤታማነት ለማሳደግ እንዲሁም የሀገራቱን ሉዓላዊነት፣ የእኩልነት እና አንዱ በሌላዉ ዉስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ ያለመግባት መርሆዎችን መሰረት በማድረግ የሀገራቱን የቆየ መልካም ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እና በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የህግ ትብብርን በተደራጀ ሁኔታ ለመምራት ታስቦ የተፈረመ ስምምነት መሆኑን ይገልፃል፡፡ ስለሆነም ስምምነቱ በወንጀል ጉዳይ የሚደረግ ምርመራን እና ክስ ሂደትን በሚመለከት ለሚደረገው የሁለትዮሽ ትብብር የሕግ ማዕቀፍን የሚፈጥር በመሆኑ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ተደርጎበት እንዲጸድቅ ለማስቻል ይህ መግለጫ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
መግቢያ. ትምህርት ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ መሆን ያለበት መሠረታዊ ሰብዓዊ መብት መሆኑ አለም አቀፍ እውቅና የተሰጠው ጉዳይ ነው፡፡ ትምህርት በማንኛውም ማህበረሰብ ውስጥ ድህነትን ለማጥፋትና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገትን ለማምጣት ምትክ የሌለው ሚና የሚጫወት መሣሪያ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ልዩ ፍላጎት ላላቸው ዜጎች ትኩረት በመስጠት በህገመንግሥቱ የዜግነት መብቶቻቸው እንዲከበሩ በተመሳሳይም የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው ውስጥ በፍትሀዊነት የትምህርት ዕድል የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲካተት አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥት ዜጎች መንግሥት ባዘጋጃቸው የአገልግሎት መስጫ ተቋማት ሁሉ እኩል የመጠቀም መብት እንዳላቸውና በተለይም ለአካል ጉዳተኞች አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፍ እንደሚያደርግ ደንግጓል (አንቀፅ 41 ንዑስ አንቀፅ 5)፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 916/2008 ውስጥ ከትምህርት ሚኒስቴር ስልጣንና ተግባራት አንዱ “የአካል ጉዳተኞች፣ አረጋውያን፣ የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችና በደማቸው ውስጥ የኤች አይ ቪ ኤድስ ያለባቸው ሰዎች በኃላፊነቱ ክልል የእኩል እድል ተጠቃሚና ሙሉ ተሳታፊ የሚሆኑበትን ሁኔታ ያመቻቻል” በሚል ተግባሩን ይገልጻል፡፡ በዚህም መሰረት የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲው አካል ጉዳተኛና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸው ህፃናትና ወጣቶች እንደችሎታቸውና ፍላጎታቸው መማር እንደሚገባቸው ይገልጻል። ይህንን እውን ለማድረግ ጥረት ቢደረግም አሁንም ቢሆን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አካል ጉዳተኛ ህፃናት፣ ወጣቶችና ጎልማሶች የትምህርት እድል ያላገኙ ስለሆነ በዚህ ተግባር ላይ አትኩሮ መስራት ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለበርካታ አመታት በአገሪቱ ውስጥ ተበታትኖ ሲሰጥ የቆየውን የልዩ ፍላጎት ትምህርት ሥርዓት ባለውና በተጠናከረ መልኩ ለመስጠት ይቻል ዘንድ በ1998 ዓ.ም የመጀመሪያውን የልዩ ፍላጎት ትምህርት ስትራቴጂ አዘጋጅቷል፡፡ ስትራቴጂውም በውስጡ ያሉትን ክፍተቶች ለመሙላት፣ በትግበራ ወቅት ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሄ ለመስጠትና ከወቅታዊ ሁኔታዎች ጋር ለማጣጣም ሲባል በ2004 ዓ.ም ተከልሷል፡፡ መንግስት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ለማዳረስ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መረጃ ሥርዓት (EMIS) እንደሚያመለክተው በ1999 የመጀመሪያ ደረጃ የትም/ እድል ያገኙት ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች ብዛት 33,300 የነበረ ሲሆን ይህ ቁጥር በ2007 ዓም 71,007 ደርሷል፡፡ በእነዚህ አመታት አንጻራዊ የቁጥር መጨመር ቢታይም ልዩ ፍላጎት ያላቸው በተለይም የአካል ጉዳተኛ ዜጎች የትምህርት ተደራሽነት አሁንም በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ለመጥቀስ በ2007 ዓም በመጀመሪያ ደረጃ የትምህርት እድል ማግኘት ያለባቸው አካል ጉዳተኛ ህጻናት ብዛት ወደ 1.86 ሚሊዮን የሚገመት ሲሆን በትምህርት ገበታ ላይ የነበሩት ግን 71,007 (3.8%) ብቻ ናቸው፡፡ይህም ሁኔታ በአጠቃላይ ልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የትምህርት አገልግሎቱ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን ያመለክታል፡፡
መግቢያ. የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌደራል ሕገ-መንግስቱ መሰረት ነጻ ፌደራላዊ የመንግስት አካል ሆኖ በአዋጅ ቁጥር 210/1992 (በአዋጅ ቁጥር 1224/2012 እንደተሻሻለው) የተቋቋመና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ የሆነ ለሰብአዊ መብቶች መስፋፋት፣ መከበርና እና ጥበቃ የሚሰራ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋም ነው። ኮሚሽኑ የተጣለበትን ኃላፊነቶች በተገቢው ሁኔታ ለመወጣት እና በ2012 ዓ.ም. ተጀምሮ በ2013 ዓ.ም. የቀጠለዉን የለውጥና የተቋም አቅም ግንባታ በተሟላ ፕሮግራም እንዲታገዝ የሚያደርግ የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አውጥቶ እየተንቀሳቀሰ ቆይቷል። ለዚሁ ዕቅድ ማስተግበሪያ የ4ኛው ዙር የፕሮግራም በጀት (2013-2015) ማዕቀፍ ላይ ተመስርቶ በየዓመቱ የተሸነሸነ መርሃ-ግብር በማዘጋጀት የተልዕኮ ስምሪቱን እየመራ ይገኛል። በዚህም መሰረት የተሻሻለውን የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት በማድረግ ተቋማዊ የለውጥ ፕሮግራም፣ የአቅም ግንባታ ስራን እንዲሁም በኃላፊነት የተሰጠውን ተግባራት አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ሪፖርት ውስጥ በ2014 በጀት ዓመት ባለፉት አስራ አንድ ወራት (01 ሐምሌ 2013 ዓ.ም. እስከ 30 ግንቦት 2014 ዓ.ም.) ውስጥ የኮሚሽኑ የዕቅድ አፈጻጸም ዘገባ ቀርቧል። ሪፖረቱ የተዋቀረው በዘጠኝ የፕሮግራም መስክ ነው። እነሱም፡-
