C/A ተግባር / አገልግሎት የሚጠበቁ ጉዳዮች ዒላማቀን የተጠናቀቀበት ቀን
የሰሜን ካሮላይና ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ የጋራ ኃላፊነት/ተጠያቂነት ስምምነት የድርጊት መርሃ ግብር/ዕቅድ መስፈርቶች
የባለጉዳይ ስም: የስደተኛ መለያ ቁጥር:
የሰሜን ካሮላይና የስደተኞች የስራ ስምሪት አገልግሎት ፕሮግራም ሁሉም ሰው ለቤተሰቡ እና ማህበረሰቡ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን ስራ በመስራት ለቤተሰቡ አስፈላጊ ነገሮችን ማቅረብ ይጠበቅበታል በሚለው ፍልስፍና ላይ መሰረት ያደርጋል። የቤተሰብ እና (ኤጀንሲው) የስራ ስምሪት አገልግሎት ባለሙያዎች ባለጉዳዩ የጋራ ኃላፊነት ስምምነቱን ካልተከተለ ይህንን የድርጊት መርሃ ግብር ያዘጋጃሉ። ደንበኛው የስራ ስምሪት እቅዱን አክብሮ እንዲቀጥል የሚወሰዱ እርምጃዎችን ይዘረዝራል።
የስራ ስምሪት ግብ:
ሌላ ግቦች:
የድርጊት መርሃ ግብር: (ደንበኛው እና የኤጀንሲው ኃላፊነቶችን ይግለጹ)
ተግባር / አገልግሎት | ዒላማ ቀን | የተጠናቀቀበት ቀን | ||
አስተያየቶች:
ይህንን የድርጊት መርሃ ግብር በጋራ እንዳዘጋጀን እና በተዘረዘሩት ኃላፊነቶች እና ቅድመ ሁኔታዎች ላይ መስማማታችንን ፊርማችን ያመለክታል።
የባለጉዳዩ ፊርማ ቀን
የኤጀንሲው የስራ ስምሪት ባለሙያ ቀን
የአስተርጓሚ ፊርማ ቀን
ወይም ትርጉም ተያይዟል
ቅፁን ለመሙላት የሚረዳ መመሪያ
የሰሜን ካሮላይና ግዛት የስደተኞች ጉዳይ ቢሮ የጋራ ኃላፊነት/ተጠያቂነት ስምምነት
የድርጊት መርሃ ግብር
ዓላማ:
የዚህ ቅጽ ዓላማ ከኤጀንሲው ጋር በመስማማት የስራ ስምሪት ዕቅድ ተዘጋጅቶለት ዕቅዱ ወደ ስራ ሲገባ ባለጉዳዩ በጋራ ኃላፊነት ስምምነት ሰነድ ውስጥ የተካተተው መመሪያን ካልተከተለ ከሁለቱም አካላት የሚጠበቁ ነገሮች እንዲሁም ኤጀንሲው ለባለጉዳዩ ያለበትን ኃላፊነት በግልፅ የሚዘረዝር መሳሪያ ለማቅረብ ነው። በጋራ ኃላፊነት ስምምነት ሰነድ ላይ እንደተገለፀው፣ ለባለጉዳዩ የሚሰጠው አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት፣ የስራ ስምሪት አገልግሎቱን የማቀናጀት ኃላፊነት የተሰጠው የስደተኞች ኤጀንሲ ባለሙያ ከባለጉዳዩ ጋር በጋራ በመሆን ቅጹን መሙላት አለበት። ቅፅ ተሞልቶ ከተጠናቀቀ በኃላ፣ የጋራ ኃላፊነት/ተጠያቂነት ስምምነት የድርጊት መርሃ ግብሩ ከከስራ ስምሪት ዕቅድ (DSS-6232) እና ከስደተኞች የጋራ ኃላፊነት/ተጠያቂነት ስምምነት (DSS-6239A) ጋር በባለጉዳዩ ፋይል ውስጥ መካተት አለበት።
መመሪዎች:
የባለጉዳይ ስም: የድርጊት መርሃ ግብሩ የሚዘጋጅለትን ባለጉዳይ ስም ያትሙ/ይፃፉ።
የስደተኛ መለያ ቁጥር: የባለጉዳዩን የስደተኛ መለያ ቁጥር ያስገቡ።
የስራ ቅጥር ግብ: በአንድ የተወሰነ ሙያ ወይም የሥራ ቅጥር ላይ ያሉ የባለጉዳዩን ምኞቶች በአጭሩ ይግለጹ።
ሌሎች ግቦች: ስልጠና እና/ወይም ዳግም የክህሎት ማረጋገጫን የሚፈልጉ ወደ ምርታማ የስራ ስምሪት ጎዳና የሚወስዱ ባለጉዳዩ ለማሳካት የመረጣቸውን ሌሎች ግቦች ያስገቡ።
የድርጊት መርሃ ግብር: የሙያ ክህሎት ስልጠና ወይም የክህሎት ማረጋገጫ ግቡን ለማሳካት ከደንበኛው እና ከኤጀንሲው የሚፈለጉ የተወሰኑ እርምጃዎችን በመዘርዘር ከዚህ በታች ያለውን ሰንጠረዥ ይሙሉ።
C/A: “C” ን ያስገቡ፣ ተግባሩ/አገልግሎቱ የደንበኛው ኃላፊነት ከሆነ።
“A” ን ያስገቡ፣ ተግባሩ የኤጀንሲው ኃላፊነት ከሆነ።
ተግባር/አገልግሎት: የሚከናወኑ የተወሰኑ ተግባራት ወይም አገልግሎትን ያስገቡ።
የሚጠበቁ ጉዳዮች: ከሚከናወኑ ተግባራት ወይም አገልግሎት የሚፈለገውን ውጤት ያስገቡ።
የታለመው ቀን: ተግባራቱ ወይም አገልግሎቱ የሚጠናቀቁበትን ቀን ያስገቡ።
የተጠናቀቀበት ቀን: ተግባራቱ ወይም አገልግሎቱ በትክክል የተጠናቀቀበትን ቀን ያስገቡ።
አስተያየቶች: ሂደቱን በተመለከተ ያሉ አስተያየቶችን እንዲሁም ሊደረጉ የሚፈለጉ ማሻሻያዎችን ወይም ክለሳዎችን ያስገቡ። የባለጉዳዩ ፊርማ: እንደ አስፈላጊነቱ ከተብራራ እና ከተተረጎመ በኋላ ደንበኛው የድርጊት መርሃ ግብሩ ላይ መፈረሙን ያረጋግጡ። ቀን: ባለጉዳዩ የድርጊት መርሃ ግብሩን የሚፈርምበትን ቀን ያስገቡ።
የስራ ባልደረባ/ባለሙያ ፊርማ: እቅዱን የሚያጠናቅቅ ባለሙያ ስምምነቱን መፈረሙን ያረጋግጡ። ቀን: ባለሙያው የድርጊት መርሃ ግብሩን የፈረመበትን ቀን ያስገቡ።
አስተርጓሚ: እቅዱ ከተብራራ እና ከተረጎመ በኋላ አስተርጓሚው መፈረሙን ያረጋግጡ (የሚመለከተው ከሆነ)። የትርጉም አገልግሎት አስፈላጊ ካልነበረ፣ እባክዎን N/A ብለው ይፃፉ።
ቀን: አስተርጓሚው የድርጊት መርሃ ግብሩን የፈረመበትን ቀን ያስገቡ።
ማስታዎሻ: የስደተኞች የጋራ ኃላፊነት/ተጠያቂነት ስምምነት የድርጊት መርሃ ግብር መስፈርቶች እቅድን የሚሞላ የአገልግሎት አቅራቢው ባለሙያ ቅፁ ተሞልቶ ሲጠናቀቅ ባለጉዳዩ የተፈረመ ቅጂ መቀበሉን ማረጋገጥ አለባቸው።
