የዓላማዎች ክለሳ የናሙና ክፍሎች

የዓላማዎች ክለሳ. የሰፈራ እና/ወይም ኑሮን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ዕቅድን ዋነኛ ዓላማዎች እና የሰፈራ ትግበራና ኑሮን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ (ለምሳሌ፡ የመጀመሪያ ደረጃና ቀጣይነት ያለው ምክከር፣ የባለድርሻ ልየታና የሕዝብ ቆጠራ ዳሰሳ ጥናቶች፣ ማሕበረ-ኢኮኖሚያዊ የመነሻ ጥናቶች፣ አሳታፊ የዕቅድ ማውጫ ስብሰባዎች፣ የሳይት መረጣ ጥናቶች፣ ለትግበራ የሚሆኑ ድርጅታዊ መዋቅሮች) እና የሒደቱ ምዘና እና የውጤት ግምገማ (ማናቸውንም ጥቅም ላይ የዋሉ አሳታፊ የክትትልና የግምገማ ስነ-ዘዴዎችን ጨምሮ) አጠቃላይ መግለጫ ማስቀመጥ፡፡ ተግባር 4፡ አበይት ግኝቶች፡ የሚከተሉትን ጉዳዮች ከግምት ውስጥ ያስገቡ፡ • መሬት ከመረከብ በፊት የቀረበ ይፋዊ መረጃና ምክክር መጠንና በመካሄድ ላይ ያለ ምክክር በቂነት • የተሰጠ ካሳ ዓይነትና የካሳው መጠን (ለምሳሌ፡ የጠፉ ንብረቶችን ለመተካት በቂ መሆን፣ የመኖሪያ ቤት ሁኔታዎች፣ ካሳ/ባለ- መብትነት፣ ገቢን ወደቀድሞ ሁኔታ መመለስና የኑሮ ዘላቂነት እርምጃዎች) • ጉዳዩ የነካቸው ሰዎች የካሳ ተመን፣ የአዲስ ሰፈራ ቦታዎችን በመለየትና የኑሮ ሁኔታን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ አማራጮችን የሚመለከቱ ውሳኔዎች ላይ ያላቸው የተሳትፎ ደረጃ • ከአካላዊ መዋቅር፣ ቦታ፣ የሐብቶችና አገልግሎቶች ተደራሽነት (ለምሳሌ፡ ጤና፣ ትምህርት፣ ውሃ እና ሳኒቴሽን፣ ትራንስፖርት፣ ማሕበራዊና የሕክምና ዋስትና፣ የግብርና እና የግጦሽ መሬት፣ የስራ ዕድሎች፣ የሥልጠና እና የማህበረሰብ ልማት ተነሳሽነቶች) በተመለከተ የምትክ ቤት በቂነት • የኑሮ ሁኔታን ወደ ቀድሞ የመመለሻ እርምጃዎች ውጤታማነት • ወደ አስተናጋጅ ማህበረሰቦች መዋሃድ • በባሕላዊ ንብረት ላይ የሚደርስ ተጽእኖ • ተጋላጭ ሰዎችና ቡድችን ለመከላከል የተወሰዱ እርምጃዎች • የቅሬታ አፈታት ሒደትና ውጤቶች ብቃት • የክትትልና ግምገማ ሒደትና ውጤቶች ተግባር 5፡ ማጠቃለያ እና አበይት ምክረ ሃሳቦች/የእርምት እርምጃዎች፡ ማጠቃለያዎችና ምክረ ሃሳቦችን፣ እንደዚሁም ማናቸውንም ክፍተቶች ወይም እልባት ያላገኙ ጉዳዮችን በጊዜ የተገደበ የእርምት ድርጊት መርሃ ግብርን ከአበይት እርምጃዎች፣ የተመደበ የሰው ሐይል፣ የመዝጊያና የበጀት የጊዜ ሰሌዳ አጠር ባለ መልኩ ማጠቃለል፡፡ የሚጠበቁ ውጤቶች - ከ RAP የሚጠበቁ ውጤቶች በግልጽ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ሊካተቱ ይችላሉ፡ • የሰፈራ የድርጊት መርሃ-ግብር • የኑሮ ሁኔታን ወደ ቀድሞ ሁኔታ የመመለስ ዕቅድ • የኦዲት ፕሮግራም ስነዳ • የቅሬታ አቀራረብ ሒደቶች የፕሮፖዛል መስፈርቶች - ይህ ክፍል ተፈላጊ የሥራ መርሃ ግብር፣ ማናቸውም የፋይናንስ መስፈርቶችን (ለምሳሌ፡ የበጀት ጣሪያ፣ የመጫረቻ ገንዘብ፣ የወጪ ክፍፍል ዝርዝሮች፣ የተለያዩ የፋይናንስና የንግድ ፕሮፖዛሎች)፣ የሚጠበቅ ድርጅታዊ ልምድ፣ የተጠቆመ የፕሮጄክት ቡድን ጥንቅርና ልምድ፣ እና አግባብነት ሲኖረውም የአካባቢ ይዘት/የአካባቢ ንዑስ ኮንትራክተር መስፈርቶችን መዘርዘር አለበት፡፡ ቅጥያ 10 የሃገር በቀል ሕዝቦች ዕቅድ የማነጻጸሪያ ነጥቦች አጠቃላይ መግለጫ ይህ ቅጥያ የሃገር በቀል ሕዝቦች ዕቅድ (IPP) የማጣቀሻ ነጥቦችን የሚዘረዝር ሲሆን ዕቅዱም በአካባቢና ማሕበራዊ ተጽእኖ ግምገማ (ESIA) ሒደት ወቅት በተለዩ ተጽእኖዎች ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡ IPP ለሚያስፈልጉት ለእያንዳንዱ ፕሮጄክት፣ CFM ከጋራ አልሚው ጋር በመተባበር የ IPP የማነጻጸሪያ ነጥቦችን ያዘጋጃል፡፡ IPP መዘጋጀት ያለበት እንደሁኔታው ተለዋዋጭ በሆነና ነገሮችን ባገናዘበ መልኩ ሲሆን የፕሮጄክቱን ዝርዝር ሁኔታና የውጤቶቹን ባህርይ ያማከለ መሆን አለበት፡፡ የ IPP ዓላማ ከባሕል አንጻር አግባብነት ባለው መንገድ በሃገር በቀል ሕዝቦች ላይ የሚደርሱ አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለመቀነስ እና/ወይም ለመካስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን መግለጽ ነው፡፡ በ IFC መምሪያ ማስታወሻ 7 መሰረት፣ በአካባቢያዎ ተጨባጭ ሁኔታዎች መሰረት፣ ራሱን ችሎ የሚቆም ሊዘጋጅ ይችላል፣ ወይም በጉዳዩ የተነኩ የሃገር በቀል ሕዝቦች ማህበረሰቦች በተመሳሳይ ሁኔታ ላይ ካሉ ማህበረሰቦች ጋር በተመሳሳይ ቦታ የሚኖሩበት ወይም ሃገር በቀል ሕዝቦች በስፋት በጉዳዩ በተነካ ሕዝብ ውስጥ የሚዋሃዱበት ሰፊ የማህበረሰብ ልማት ዕቅድ አካል ሊሆን ይችላል፡፡ የ IPP የማነጻጸሪያ ነጥቦች አነስተኛ መስፈርቶች ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡