የኦዲት ዕቅድ የናሙና ክፍሎች

የኦዲት ዕቅድ. ዓመታዊ ዕቅድ የሚዘጋጅ ሲሆን ይህም ዕቅድ የሚካሄዱ ኦዲቶችን፣ ኦዲት የሚደረጉ ድርጅቶችን (ኮርፖሬት፣ ፕሮጄክት፣ ሐብት) እና የኦዲቶቹን መርሃ ግብር ያስቀምጣል፡፡ የቀጣዩ ዓመት ዕቅድና የጊዜ ሰሌዳ በዓመታዊ የሥራ አመራር ግምገማ ስብሰባ ወቅት ለከፍተኛ ሥራ አመራር ቡድን ቀርቦ በከፍተኛው ሥራ አመራር የሚጸድቅና የሚፈረም ይሆናል፡፡ የኮርፖሬት ደረጃ ESMS ኦዲቶችን በተመለከተ፣ ኦዲቶቹ ቢያንስ በየዓመቱ ይካሄዳሉ፡፡ በፕሮጄክት ደረጃ የሚካሄዱ ኦዲቶች ድግግሞሽ የሚመሰረተው በፕሮጄክቱ የስጋት አመዳደብ፣ ማናቸውም የሕግ አስፈላጊ ሁኔታዎችና ማናቸውም ከራሱ ከፕሮጄክቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ታሳቢ ሁኔታዎች ላይ ነው፡፡ 6.