የESG አስተዳደር የናሙና ክፍሎች

የESG አስተዳደር. CFM እንደ ESG አስተዳደር የማዕከላዊ ቢሮ ቡድን፣ ሁሉንም የE&S ግዴታዎችን እና ኃላፊነቶንች ለመጠበቅ እና ለመፈጸም በገንዘብ ደረጃ እንዲሁም እንደ ፕሮጄክት ድርጅት ደረጃ፣ በዚህ በESMS ውስጥ እንደተገለጸው ግለሰብን ሿሟል። የESG የበላይ ኃላፊ በቀጥታ ለCFM ቦርድ የተመደበው አባል የE&S የተሰራውን ኃላፊነቶች ሪፖርት ያደርጋል። የሥራ ግለታሪክ በየጊዜው እንደሚገነባ፣ የCFM የESG ሠራተኛ የE&S ቀጣይ ውጤታማነት ገማች እና ቁጥጥርን ለማረጋገጥ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ሊስፋፋ ይችላል። የሚናዎች እና የኃላፊነቶች ክፍፍሎች በESG የበላይ ባለሥልጣኖች መካከል እና ተጨማሪ የESG ሠራተኛ በማንኛውም ጊዜ ወደፊት እንደሚቀጥር ይህ በESG ውስጥ ይገለጽ እና መደበኛ ይሆናል። የኢንቨስትመንት ኮሚቴ፡ ጠቃሚነት ያለው የCIO የገንዘብ ኢንቨስትመንት ኮሚቴ ማንኛውም የኢንቨስትመንት ውሳኔ ከሚደረገው በፊት (ለማንኛውም ሦስት የገንዘብ ድጋፍ) ለሁሉም የአከባቢያዊ እና ለማኅበራዊ ሕይወት ስጋት እርግጠኛ ለመሆኑ ኃላፊነቱ የሚወስድ ሲሆን፣ ተጽእኖዎቹ በተገቢ ሁኔታ እንዲገመገም፣ እና ስጋቱም በCFM ውስጣዊ የስጋት አስተዳደር ትንታኔ እና የውሳኔ ሂደትን በሙሉ ይደባለቃል። የኢንቨስትመንት ሠራተኛ፡ (ለልማት እና ለግንባታ እኩልነት የገንዘብ ድጋፍ ይተገበራል) ሁሉም የኢንቨስትመንት ሠራተኞች ከESG አስተዳደር ጋር ሁሉም የፕሮጄክቶች በዚህ ESMS ላይ የተቀመጠው ግዴታዎች መሰረት መልማታቸውን እና ተፈጻሚ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በጋራ ኃፊነት የሚወስዱ ይሆናሉ። ሁሉም ሠራተኞች የE&S ጠቃሚ መረጃ እስከተቻለው ድረስ ለመውሰድ እና ለመስጠት፣ የE&S አጋዥ ትንታኔ እና የምልከታ ሂደቶችን፣ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን ለማጠናከር እና ለማገዝ፣ እና በማንኛውም የፕሮጄክት ድርጅት ደካማ አፈጻጸም ላይ ለመስራት ኃላፊነትን በጋራ ይወስዳሉ። የቋም ንብረት አስተዳደሮች፡ (መልሶ በገንዘብ ለመደገፍ ተግባራዊ ይሆናል) ሁሉም የቋሚ ንብረት አስተዳደሮች (እንደ 'ኢንቨስትመንት ባለሥልጣኖች' ሊገለጽ የሚልች) በዋናነት ኃላፊነቱ በCFM ፈንታ ቋሚ ንብረቶችን ለመቆጣጠር መሆን ያለበት ሰው የE&S ስጋቶች እና አስተዳደር ከዚያ ቋሚ ንብረት ጋር የሚያያዘው ጋር የቀን ለቀን ቁጥጥር ለማድረግ ኃላፊነት አለበት። የቋሚ ንብረት አስተዳዳሪዎች ጉዳዮችን ለCIO የገንዘብ ድጋፍ የESG አስተዳደርን፣ በዚህ ESG ውስጥ በተቀመጡት ግዴታዎች መሰረት ግንኙነት ማድረግ ኃላፊነታቸው ነው። E&S የውጪ አማካሪዎች፡ CFM የውጪ አማካሪዎችን፣ የCIO ገንዘብ እና/ወይም የፕሮጄክት ድርጅትን ስለ ትጋት፣ ቁጥጥር እና/ ወይም ከCIO ገንዘብ ጋር በተያያዘ የገንዘብ ሥራ ላይ ማዋል ምክርን ለመስጠት ሠራተኛ ይቀጥራል። ይህ ድጋፍ በCFM የESG አስተዳደር ይገለጻ፤ ይመቻች እና ቁጥጥር ይደረግበታል። የE&S አመራር የሚያመቻቸው የፕሮጄክት ደርጃ CFM ለሁሉም ፕሮጄክቶች በE&S አመራር ውስጥ የመምራት ሚናውን ይወስዳል። የፕሮጄክቱ ድርጅቶች የፕሮጄክታቸውን የአከባቢያዊ እና የማኅበራዊ ሕይወት ስጋቶችን እንደዚህ ESMS ግዴታዎች መሰረት ለማስተዳደር ኃላፊነት አለባቸው። እያንዳንዱ የፕሮጄክቱ ድርጅት ተገቢ የሆነ እና ለቦታው ብቁ የሆነ ሠራተኛ፣ በተለይም ለፕሮጄክቱ የE&S አመራር ዕቅዶች፣ እና በስኬታማነት ሁሉንም አከባቢያዊ እና የማኅበራዊ ሕይወት ማቅለያ መለኪያዎች ለመቆጣጠር እና ተግባራዊ ለማድረግ ሀብት እንዳላቸው ማረጋገጥ አለባቸው። እንደ CFM በፕሮጄክት ድርጅቶች የአመራር ቦርድ ውስጥ የግለሰቦች መቀመጫ እንደሚኖሩ መጠን፣ CFM በE&S ጉዳዮች ላይ እቅጣጫ ለመስጠት እና ለመምራት ይችላል። የCFM የESG አመራር በተገቢ ሁኔታ የሰለጠነ እና ብቁ የሆነ የE&S ፕሮጄክት አስተዳደር ለመቅጠር በቅርበት ከፕሮጄክት ድርጅት አመራር ጋር ይሰራል። የCFM የESG አመራር የE&S አመራር ሁኔታዎችን በፕሮጄክት ደረጃ ይመለከት እና ከዚህ የESMS ግዴታዎች ጋር መስማማቱን እና ከሌሎች የE&S ተባባሪ ግዴታዎች ጋር መስማማቱን ያረጋግጣል። የE&S ፕሮጄክት አስተዳደር ለCFM የESG አመራር ተጠያቂ ይሆናል። የአመላካቺ የድርጅት ሠንጠረዥ በፕሮጄክት ድርጅቶች ውስጥ የE&S ኃላፊነቶች ከዚህ በታች የቀረቡት ላይ ድምቀት ይሰጣል። ሥዕል4.1