ተከሳሾች የናሙና ክፍሎች
ተከሳሾች. በበኩላቸው ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም የቤት ሽያጭ ውል መደረጉ የሚካድ አይደለም፤ በውሉ መሰረት በዕለቱ ከሳሽ ብር 650,000/ስድስት መቶ ሀምሳ ሺህ/ ቀብድ ለመክፈል ተስማምተው የከፈሉ ሲሆን ቀሪውን የቤት ሽያጭ ገንዘብ በውሉ በተመለከተው አግባብ ሰኔ 18 ቀን ብር 4,000,000/አራት ሚሊዮን/፣ ሐምሌ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ደግሞ ብር 3,000,000/ሶስት ሚሊዮን/ ለመክፈል የተስማማን ቢሆንም ከሳሽ በውሉ በተመለከተው ሁኔታ ገንዘቡን በመክፈል ሀላፊነታቸውን አልተወጡም፡፡ በውሉ በተመለከተው አግባብ መክፈል ሲጠበቅበት ይህን ግዴታዉን ሳይወጣ በመቅረቱ ዉሉን ያፈረሰዉ ከሳሽ ራሱ እንጂ ተከሳሾች አይደለንም፡፡ ከሳሽ በዉል ላይ በተቀመጠዉ ጊዜ ክፍያ ባለመክፈሉ የተነሳ ተከሳሾች ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም ማስጠንቀቂያ የሰጠነዉ ቢሆንም በማስጠንቀቂያዉ መሠረትም ግዴታዉን ሳይወጣ ቀርቷል፡፡ ከሳሽ በክስ አቤቱታዉ ላይ ብር 2,000,000(ሁለት ሚሊየን ብር) በቀብድነት እንዲላክላቸዉ በተደረገዉ ስምምነት በ2ኛ ተከሳሽ በአቢሲኒያ ባንክ መካኒሳ ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥራቸዉ ሰኔ 29 ቀን 2013ዓ.ም ገቢ አድርጊያለሁ ቢልም በዉላችን ላይ ስለ ሁለት ሚሊየን ብር ክፍያ ጭራሹኑ የሌለ ከመሆኑም በተጨማሪ ቀደም ሲል የፈጸምነዉ በሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም የሽያጭ ውል በጽሁፍ እንደመደረጉ መጠን ይህን ዉል በሌላ ጽሁፍ ዉል ስለመተካቱ ያቀረበዉ ምንም ማስረጃ በሌለበት ከሳሽ በራሱ ጊዜ ሊያዉም ተከሳሾች ማስጠንቀቂያ ከሰጠንበት እንዲሁም በዉሉ ላይ ከተቀመጠዉ ቀናት እና የገንዘብ መጠን ዉጪ ተከሳሸ ገቢ ያደረገዉ ብር 2,000,000.00(ሁለት ሚሊየን) በምንም መልኩ በዉሉ መሠረት ከሳሽ ግዴታዉን ተወጥቷል ሊያሰኝ አይችልም፤ ይህን ብር ከሳሽ ካስገባ በኃላ በቅንነት ከዉላችን ዉጪ ያስገባዉን 2,000,000ብር(ሁለት ሚሊየን ብር) መዉሰድ ትችላለህ፤ይመለስልህ ስንለዉም ከሳሽ ፈቃደኛም አልነበረም፡፡ አሁንም ቢሆን ይህን ከሳሽ ከዉል ዉጪ ገቢ ያደረገዉን 2,000,000ብር(ሁለት ሚሊየን ብር) መዉሰድ ይችላል፡፡ በመሆኑም በሰኔ 17 ቀን 2013ዓ.ም የተጻፈዉ ዉል ያፈረሰዉና ያልፈጸመዉ ከሳሽ ራሱ በመሆኑ በፍ/ሕ/ቁጥር 1885(2) መሰረት በዉሉ መሠረት ያልተፈጸመዉ ወይም ዉሉን ያፈረሰ ከሳሽ በመሆኑ በዉል ላይ የተጠቀሰዉን ቀብድ ከሳሽ መጠየቅ ስለማይችል የተከበረዉ ፍ/ቤት የከሳሽን ክስ ዉድቅ በማድረግ ዉሳኔ እንዲሰጥልን በከሳሽና ተከሳሸ መካከል ግልጽ ዉል ባለበት እና የቀብድ ገንዘቡም መጠን በግልጽ ተቀምጦ ባለበት ከሳሽ ሆነ ብሎ የቀበድ ገንዘቡ ብር 2,650,000(ሁለት ሚሊየን ስድስት መቶ ሀምሳ ሺህ) በማለት ያቀረበዉ ክስ አግባብነት የሌለዉና የቀብድ ዉል ህግጋትን የጣሰ ነዉ፡፡ ዉል ለመለወጥም ሆነ ለማሻሻል ወይም ተጨማሪ ዉል ለማድረግ በፍ/ሕ/ቁጥር 1722 መሠረት በጽሁፍ መደረግ እንደሚገባዉ ከተደነገገዉ የህግ ደንጋጌ አንጻርም የከሳሽ የክስ ፍሬ ነገር የሕግ ድጋፍ የለዉም፡፡ በመሆኑም የተከበረዉ ፍ/ቤት ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም በተፈጸመዉ ዉል መሠረት የቀብድ ገንዘብ መጠኑ ብር 650,000(ስድስት መቶ ሀምሳ ሺህ) እንጂ ብር 2,650,000(ሁለት ሚሊየን ስድስት መቶ ሀምሳ ሺህ) አይደለም እንዲባልልን፣ ከሳሽ በክሰ አቤቱታዉ ላይ በሰኔ 17 ቀን 2013ዓ.ም በተጸፈመ የቤት ሽያጭ ዉል መሠረት ተከሳሾች ቀሪ ገንዘባቸዉን 5,000,000ብር(አምስት ሚሊየን ብር) ተቀብለዉ ቤቱንና የቤቱን ሰነድ በህግ ሀይል ተገደዉ እንዲያስረክቡኝ እና ወደ ሚመለከተዉ መንግስታዊ አካል ቀረበዉ ስመ ሀብቱን እንዲያዛዉሩ በማለት ያቀረበዉ ክስ ከላይ በዝርዝር እንዳቀረብነዉ በዉሉ መሠረት በከሳሽ በኩል የሚጠበቀውን ግዴታ ሳይወጣ ተከሳሾች በውሉ የተመለከተ ግዴታቸውን እንዲወጡ ሊጠይቅ አይችልም በሚል ክርክር ያቀረቡ ስለመሆኑ ከመዝገቡ መረዳት ይቻላል፡፡ ከሳሽ የክስ አቤቱታቸውን ለማስዳት የሰውና የሰነድ ማስጃዎችን አያይዘው ያቀረቡ ሲሆን በሰነድ ማስረጃዎች ረገድ ግራ ቀኙ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረጉትን የመኖሪያ ቤት ሽያጭ ውል፣ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን የካርታ ቁጥሩ 03/263/0017225/00 የሆነና በ1ኛ ተከሳሽ ስም የተሰጠ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታን፣ 1ኛ ተከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ የሰጡትን ሕጋዊ ውክልና፣ ከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ ብር 2,000,000/ሁለት ሚሊዮን/ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ ደረሰኝ እንዲሁም ከሳሽ በጠበቃቸው በኩል ለተከሳሾች የሰጡት ሕጋዊ ማስጠንቀቂያን በሰነድ ማስረጃነት አያይዘው አቅርበው በፍርድ ቤቱ ተመርምሯ...
