ቅጣትን ተግባራዊ ማድረግ /Implementation of Sanctions/ የናሙና ክፍሎች

ቅጣትን ተግባራዊ ማድረግ /Implementation of Sanctions/. በአንድ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ቅጣት ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት የማኅበሩ አመራር ሁልጊዜም ማረጋገጥ ያለባቸው ጉዳዮች፤ • የቀረበው ቅጣት አድሎና ጥላቻ የሌለበት መሆኑን፣ • የቀረበው ቅጣት በደንብ የተተነተነ እና ምክንያታዊ መሆኑን፣ • ትክክለኛ አስተዳደረዊ ሂደቱን የተከተለ መሆኑን ማየት ይገባቸዋል፡፡ የቅጣት እርምጃ ከተወሰደ በኋላ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር አመራር አካላት ተፈጻሚ እንዲሆን ጥረት ማድረግና ግልጽ በሆነ ስህተት ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ቀድም የተወሰነው ውሳኔ በተጽዕኖ እንዳይቀየር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር በአጥፊዎች ላይ የተወሰነውን ቅጣት ተግባራዊ ለማዳረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ፤ በመስኖ አውታሩ አሰራርና ጥገና ስራ እና/ወይም በመስኖ ውሃ ማኅበሩ አመራር በራሱ ላይ ከፍተኛ የሆነ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ የማኅበሩ አባላትና አባል ያልሆኑ ተጠቃሚዎች በተከሰቱ ጥፋቶች ላይ የተወሰነው የቅጣት ውሳኔ በትክክል ተግባራዊ ካልተደረገ ህግና ደንቦችን ያለመቀበል