ቅሬታ አቅራቢው የናሙና ክፍሎች

ቅሬታ አቅራቢው. ቅሬታውን ባቀረበ በ7 ቀናት ውስጥ ጉዳዩን ለመፍታት የሚወሰድ የእርምት እርምጃን የሚዘረዝር ማረጋገጫ ይሰጠዋል፡፡ ከዚያም የሚመለከታቸው ወገኖች የእርምት እርምጃውን ይተገብራሉ፡፡ ቅሬታውን ለመዝጋት የሚቀመጠው የጊዜ ገደብ በተቻለ መጠን አጭር መሆን ያለበት ሲሆን ቅሬታው በመጀመሪያ ከቀረበበት ቀን አንስቶ 20 ቀናት ቢሆን ይመከራል፡፡ ማንኛውም መዘግየት የሚፈጠር ከሆነ ቅሬታ አቅራቢው እንዲያውቀው ይደረጋል፡፡ ቅሬታ አቅራቢው ላቀረበው ቅሬታ በተሰጠው መፍትሔ ደስተኛ ካልሆነ ለገለልተኛ ፓናል ይግባኝ የመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን ይህም ፓናል እንደ ጠበቃ፣ የፕሮጄክት ተወካዮች፣ የመንግስትና የማህበረሰብ መሪዎች የመሳሰሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላትን ያቀፈ ነው፡፡