መሬት ማግኘትና በፍቃደኝነት ላይ ያልተመሠረተ አሰፋፈር የናሙና ክፍሎች

መሬት ማግኘትና በፍቃደኝነት ላይ ያልተመሠረተ አሰፋፈር. ሲኤፍኤም በተቻለው ሁሉ በፕሮጀክቱ የሚነኩ ሰዎች በፍቀደኝነት ላይ ያልተመሠረተ አካላዊ እና/ወይም ኢኮኖሚያዊ መፈናቀል ለማስቀረት ተግቶ ይሠራል። ፕሮጀክቱ የሚነካቸው ሰዎችን አካላዊ እና/ወይም ኢኮኖሚያዊ መፈናቀል የማስከተል የኢንቨስትመንቱ ችሎታ በተቻለ መጠን በጥንቃቄ ሂደት ወቅት እልባት የሚያገኝ ይሆናል። በግል ለተያዙ ሀብቶች (በባሕላዊ እና በልማዳዊ መብቶች የሚተዳደሩትን ጨምሮ) እና የጋራ ንብረት የሆኑ ሀብቶችና የተፈጥሮ ሀብቶች ትኩረት የሚሰጥ ይሆናል። አካላዊ ወይም ሌላ ውስብሰብ መልሶ ማስፈር ከተፈለገ ኢንቨስትመንቱ “ሀ” (በጣም ከፍተኛ) የስጋት ደረጃ ይሰጠዋል (ክፍል 5ን ይመልከቱ)። በማንኛውም ኢኮኖሚያዊ አሰፋፈር ባህሪ መሠረት ኢንቨስትመንቱ “ሀ” (ከፍተኛ) ወይም “ለ+” ተደርጎ ሊመደብ ይችላል። አካላዊ እና/ወይም ኢኮኖሚያዊ አሰፋፈር የማይቻል ከሆነ በአይኤፍሲ ፒኤስ5 አላማዎች መሠረት በሲአይኦ ፈንድ ኢንቨስት የተደረጉ ሁሉም ፕሮጀክቶች፦ • አማራጭ የፕሮጀክት ሲዛይን በመፈለግ መፈናቀልን መቀነስ፤ • በማስገደድ ላይ የተመሠረተ ማፈናቀልን ማስቀረት፤ • (i) ለጠፋው ሀብት ምትክ ካሳ በመስጠት እና (ii) የመልሶ ማስፈር ሥራ መረጃ በመስጠት፣ በማማከር እና ፕሮጀክቱ በሚነካቸው ሰዎች በመረጃ ላይ የተመሠረተ ተሳትፎ መሠረት የተፈጸመ መሆኑን በማረጋገጥ ከመሬት አወሳሰድ እና በመሬት አጠቃቀም ገደቦች የሚመጣውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖዎች መተንበይ እና ማስወገድ ወይም ማስወገድ ካልተቻለ መቀነስ፤ • የተፈናቀሉ ሰዎችን የኑሮ ደረጃ እና አኗኗር ማሻሻል ወይም ወደነበረበት መመለስ፣ እና • እንደመልሶ ማስፈሪያ ቦታ የይዞታቸውን ደኅንነት በመጠበቅ በቂ ቤት በመስጠት በአካል የተፈናቀሉ ሰዎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል። በኢኤስአይኤ መሠረት ፕሮጀክቱ አካላዊ መፈናቀልን የሚያስከትል ሆኖ ከታየ ሲኤፍኤም የመልሶ ማስፈሪያ ተግባር እቅድ እንዲዘጋጅ ያስገድዳል። አባሪ 9 በአይኤፍሲ ፒኤስ5 መሠረት የሚዘጋጀውን የመልሶ ማስፈር ተግባር እቅድ አዘገጃጀት የአሠራር መመሪያ (ቲኦአር) ይሰጣል። እንዲህ ዓይነቱ የአሠራር መመሪያ የመልሶ ማስፈሪያ ተግባር ዕቅድ በአይኤፍሲ ዝርዝር የተቀመጡትን ስምምነቶች የሚያሟላ ዝግጅት ዝቅተኛውን ደረጃ የሚከተሉትን ጨምሮ ሥራ ላይ የሚውል ይሆናል፦ • ፕሮጀክቱ የሚነካቸው ሰዎች ለመልሶ ማስፈሪያና ለካሳ ድጋፍ ለማግኘት መቻል አለመቻላቸውን ለመወሰን የብቃት መስፈርት፦ • የጠፋን ንብረት ዋጋ ግምትና ካሳ ለመገመት መከተል የሚኖርበት ዘዴ2፤ • የባለመብትነት ማእቀፍ (ጉዳት ለደረሰባቸው የተለያዩ ሰዎች ምድብ)፤ • ለተፈናቀሉ ሰዎች በመሬት ላይ፤ በደመወዝ እና በድርጅት ላይ በመመርኮዝ ወደ ቀድሞ ህይወታቸው ለመመለስና ኑሮአቸውን ለማሻሻል የሚወሰዱ እርምጃዎች፤ • መልሰው የሚሰፍሩባቸውን ሳይቶች መምረጥና አማራጭ ሳይቶችን ግምት ውስጥ ማስገባት፤ • ከይዞታ ደኅንነትና ከመልሶ ማስፈር እገዛ ጋር የቤት ምርጫ ማቅረብ • የቤት መሠረተ ልማት (ለምሳሌ የውሀ አቅርቦት፤ ፍሳሽ ቆሻሻ) እና ማህበራዊ አገልግሎቶች (ለምሳሌ የጤና ክሊኒክ፤ ትምህርት ቤት፤ መንገዶች) የሚለሙበትና የሚቀርቡበት ዝርዝር ዕቅድ፤ • የማኅበረሰብ ስምሪት (በአይኤፍሲ ፒኤስ1 እና በአይኤፍሲ ፒኤስ7 ለነባር ሰዎች ከታች ያለውን ይመልከቱ) እና የቅሬታ አቀራረብ ሂደቶች አቅርቦት፤ • የመልሶ ማስፈሩን ሂደት ለመቆጣጠር የሚያስችል ድርጅታዊ አሠራር፤ • በመልሶ ማስፈር ተግባር ዕቅድ ድንጋጌዎች መሠረት መፈፀሙን ለማረጋገጥ ከመልሶ ማስፈር ሂደቱ ጋር በተያያዘ ቀጣይነት ያለው ቁጥጥርና ሪፖርት ማድረጊያ ዝርዝር ማውጣት፤ እና • በመልሶ ማስፈሪያ የተግባር ዕቅድ ውስጥ የተዘረዘሩት ሁሉም ዝርዝር ተግባራት በአጥጋቢ ሁኔታ ምላሽ ካገኙ የማጠናቀቂያ ምርመራ የሚደረግበት አካሄድ። 1 ለሕግ አስከባሪ መኮንኖች በተቀመጠው የተባበሩት መንግሥታት የስነ-ምግባር ደንብ እና በሕግ አስከባሪ መኮንኖች የሀይል እና መሳሪያ አጠቃቀም ላይ በተቀመጠው የተባበሩት መንግሥታት መሠረታዊ መርሆዎች መሠረት። 2 ይህም ማንኛውም የተለዩ መስፈርቶችን ማለትም የመሬት ይዞታ ባለቤትነት፣ የይዞታ ዘመን፣ በመንግሥት የተመራ የመሬት አያያዝ ሂደት እና ማንኛውም በፕሮጀክት ኩባንያው ሙሉ የመተኪያ ወጪ የሚያገኝበትን ተጨማሪ እርምጃዎችን ጨምሮ የሀገሪቱን የሕግ ማእቀፍ ማካተት ይኖርበታል። የኢኮኖሚ መፈናቀልን ማስቀረት በማይቻልበት ሁኔታ ወደነበሩበት ህይወት የመመለሻ ዕቅድ መዘጋጀት አለበት። በአይኤፍሲ ፒኤስ1 መሠረት የእንዲህ ዓይነቶቹ እቅዶች ዝግጅት በመረጃ ...