መልመጃ እና ጭውውት የናሙና ክፍሎች

መልመጃ እና ጭውውት. ስልጠናው ከተሰጠና ገለጻ ከተደረገ በኋላ፣ አሰልጣኙ የስብሰባ ቃለጉባኤ እንዴት ሊዘጋጅ እንደሚችል ማሳየት አለበት፣ • አሰልጣኙ አሰራሩን ካሳየ በኋላ፣ ሰልጠኞች ባገኙት ክህሎት መሰረት የስብሰባ ቃለጉበኤ የማዘጋጀት ዕድል ማግኘት ወይም መልመጃ እንዲሰሩ መደረግ አለበት፣ • የስብሰባ ቃለጉባኤ ምሳሌ በዕዝል-ሀ ይመልከቱ፣ 🗐 ስልጠናው ከጠናቀቀ በኋላ ስለ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ አዘገጃጀት ዋና ዋና ጉዳዮችን በአጭሩ ሊገልጽ የሚችል ማኑዋል ሁሉም ተሳታፊዎች እንዲያገኙ አድርግ፡፡ ዕዝል-ሀ፡ የሰብሰባ ቃለ ጉባኤ (ምሳሌ) የመስኖ ውሃ ተጠቃሚዎች ማኅበር ስም፣………………………….ቀን፣……………………… የሰብሳባው ዓይነት፣ ወርሃዊ የኮሚቴ አባላት ስብሰባ፣ የሰብሰባው ተሳታፊዎች፣ • ………………………………….የማኅበሩ ሊቀመንበር • ………………………………….የማኅበሩ ም/ሊቀመንበር • ………………………………….የማኅበሩ ፀሀፊ • ………………………………….የማኅበሩ ገንዘብ ያዥ • ………………………………….የኮሚቴ አባል • ………………………………….የኮሚቴ አባል • ………………………………….የኮሚቴ አባል በስብሰባው ያልተገኙ፣ • ………………………………….የኮሚቴ አባል • ………………………………….የኮሚቴ አባል የስብሰባው መሪ…………………………….የማኅበሩ ሊቀመንበር የስብሳባው አጀንዳ፣ • ስብሰባውን በማኅበሩ የስብሰባ መሪ/ሊቀመንበር መክፈት፣ • በማኅበሩ ፀሀፊ ተሳታፊዎችን መመዝገብ፣ • አጀንዳዎችን በማኅበሩ ሊቀመንበር/ፀሀፊ እንዲቀርቡ በማድረግ ማጽደቅ፣ • ያለፈውን የማኅበሩን የስብሰባ ቃለጉባኤ በማኅበሩ ሊቀመንበር/ፀሀፊ ማቅረብና ማጽደቅ፣ • አዲስ የመስኖ ቴክኒሻን መቅጠር፣ • የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ፣ • ግምገማ እና ውይይት ማካሄድ፣ • የጥያቄ ጊዜ፣ እና • በማኅበሩ ሊቀመንበር/ሰብሳቢ ስብሳባውን መዝጋት፣ ማጠቃለያ 1. ያለፈው ወርሃዊ ሰብሰባ ቃለ ጉባኤ ምንም ለውጥ ሳይደረግበት ፀድቋል፡፡ 2. የአቶ……………………የመስኖ ቴክኒሻን የቀጣይ ስድስት ወራት ቅጥር ከ………ቀን ……….ዓ.ም ጀምሮ በወር ብር……….. እየተከፈለው እንዲሰራ በሁሉም የስራ አመራር ኮሚቴ አባላት ፀድቋል፡፡ 3. ለማህበሩ አገልግሎት እንዲውሉ የተጠየቁ የ25 ማስታወሻ፣ 10 የፋይል አቃፊያዎች ግዥ በሁሉም የስራ አመራር ኮሚቴ ፀድቋል፡፡ 4. አቶ …………………… ለብሎክ 5 የሚሰጠው የመስኖ አገልግሎት መቋረጥ የለበትም ሲል ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ሁሉም የስራ አመራር ኮሚቴ የመሰኖ ቴክኒሻኑ አፋጣኝ የጥገና ስራ መስራት እንደላበት ወስኗል፡፡ 5. የስራ አመራር ኮሚቴው ወርሃዊ የስብሰባ ቀን ለ………………..እንዲሆን ታቅዷል፡፡ ቃለጉባኤውን ያዘጋጀው፣…………………… /የማኅበሩ ፀሀፊ/ ፊርማ……………… ቃለጉባኤውን ያፀደቀው፣…………………… /የማኅበሩ ሊቀመንበር/ ፊርማ……………. 3.3