የተሻሻሉ ትርጓሜዎች እንዲሁም ምሳሌ አንቀጦች

የተሻሻሉ ትርጓሜዎች. 3.1 የሚከተሉት ቃላትና ሐረጎች በረቂቅ አዋጁ ትርጓሜ ዉስጥ ተሻሽለዉ እንዲካተቱ ተደርገዋል፡- ▪ አሁን በሥራ ላይ ባለዉ አዋጅ ንኡስ አንቀፅ 2(12) ለ‹የፋይናንስ ተቋም› የተሰጠዉ ትርጓሜ የጠለፋ መድን ሰጪን፣ የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድ አዉጪንና የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተርን ባካተተ መልኩ በረቂቅ አዋጁ ንኡስ አንቀፅ 2(32) እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ ▪ አሁን በሥራ ላይ ባለዉ አዋጅ ንኡስ አንቀፅ 2(18) ለ‹ኦፕሬተር› የተሰጠዉ ትርጓሜ የክፍያ ትእዛዝን ወይም የመንግስት የዋስትና ሰነዶችን የሚያስተላልፍ፣ የሚያቻችል፣የሚያጣራ፣ የተጣራ የመጨረሻ ተከፋይ ሂሳብን የሚወስን እና የሚያወራርድ ስርዓትን እንዲያቋቁምና እንዲሰራ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ወይም ይሁንታ የሰጠውን ሌላ ማንኛውንም ኩባንያ በሚያካትት ሁኔታ በረቂቅ አዋጁ ንኡስ አንቀፅ 2(34) ‹የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር› ተብሎ እንዲሻሻል ተደርጓል፡፡ II.