አዲስ ድንጋጌዎች እንዲሁም ምሳሌ አንቀጦች

አዲስ ድንጋጌዎች. 3.4 አሁን በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ንዑስ አንቀጽ 4(1)(ለ) ተሰርዞ ለመንግስት ሰነዶች ማዕከላዊ የሰነደ ሙዓለ-ንዋይ ግምጃ ቤትን የማቋቋም፣ ተዛማጅ መመሪያና ዉስጠ ደንብ የማዉጣትና ሰነደ ሙዓለ- ንዋዮቹንም የመመዝገብ ብቸኛ ሥልጣን የብሔራዊ ባንክ እንደሆነ በረቂቅ አዋጁ ተመሳሳይ ንኡስ አንቀፅ በአዲስ መልክ እንዲደነገግ ተደርጓል፡፡ 3.5 አሁን በሥራ ላይ ያለዉ አዋጅ ንኡስ አንቀፅ 4(2)(ሀ) ተሰርዞ ለክፍያ ሥርዓት ኦፕሬተር እና ለክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪ ፈቃድ ወይም ይሁንታ የመስጠት ሥልጣን የብሔራዊ ባንክ እንደሆነ በይበልጥ ገላጭ በሆነ መልኩ በረቂቅ አዋጁ በተመሳሳይ ንኡስ አንቀፅ በአዲስ መልክ እንዲደነገግ ተደርጓል፡፡ 3.6 አሁን በሥራ ላይ ያለው አዋጅ ንዑስ አንቀጽ 4(2)(መ) ተሰርዞ ተሳታፊዎች፣ የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አውጭዎችና የክፍያ ስርዓት ኦኘሬተሮች የሥርዓቱን መሠረተ ልማት ግንባታና ተናባቢነት የሚመለከቱ ኢንቨስትመንቶችንና ወጪዎችን ስለሚጋሩበት ሁኔታ፣ ስለሚያስከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ መጠን እንዲሁም ከኤሌክትሮኒክ ሂሳብና ግብይት እንዲሁም ከወኪልና ከሌላ ኤሌክትሮኒክ መሳሪያ በጥሬ ገንዘብ ወጪ ከማድረግ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ጣሪያዎችን የመወሰን ሥልጣን ብሔራዊ ባንክ እንደሚኖረዉ በረቂቅ አዋጁ በተመሳሳይ ንኡስ አንቀፅ በአዲስ መልክና በተብራራ ሁኔታ ተደንግጓል፡፡ 3.7 አሁን በሥራ ላይ ያለዉ አዋጅ አንቀፅ 5 አደዲስና ነባር ንዑስ አንቀፆችን በማካተት ተሻሽሏል፡፡ የአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5(1) ተሰርዞ ከብሔራዊ ባንክ በስተቀር ሌላ ማንኛውም ሰው ከባንኩ ፈቃድ ወይም ይሁንታ ሳያገኝ የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አውጪ ወይም የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር መሆን እንደማይችል በረቂቅ አዋጁ ተመሳሳይ ንዑስ አንቀፅ በተብራራ ሁኔታ በአዲስ መልክ እንዲደነገግ ተደርጓል፡፡ 3.8 ከብሔራዊ ባንክ በቅድሚያ የፅሑፍ ፈቃድ ካላገኘ በቀር ማንኛዉም የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር ወይም የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪ አዲስ የክፍያ ስርዓት መዘርጋት ወይም አዲስ የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ ማዉጣት፣ ከሌላ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር ወይም የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪ ጋር መቀላቀል ወይም የሌላ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተርን ወይም የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪን ሥራ በባለቤትነት መያዝ፣ በመቀላቀልም ሆነ በሌላ መንገድ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተሩን ወይም የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪዉን መሸጥ ወይም የባለሀብትነት መተላለፍ የሚያስከትሉ ማናቸዉንም ዓይነት ስምምነቶች ወይም ዉሎች ማድረግ ወይም የተፈቀደለትን የሥራ ዓይነት መቀየር፣ ራሱ ያወጣዉን አክሲዮን መልሶ መግዛት ወይም በመደበኛ ተግባሩ በተከሰተ ኪሳራ ምክንያት ካልሆነ በቀር ካፒታሉን መቀነስ፣ የመመስረቻ ፅሁፉን ማሻሻል ወይም ሥራዉን እንዲያካሂድ ፈቃድ ያገኘበትን ስም መቀየር እንደማይችል በረቂቅ አዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5(3) በተዘረዘረና በአዲስ መልክ እንዲደነገግ ተደርጓል፡፡ 3.9 የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪ ወይም የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር በማንኛዉም ጊዜ አግባብነት ያላቸዉን በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብን እና ሽብርተኛን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጡ የሀገሪቱን ህጎች ማክበርና መተግበር እንደሚኖርበት በረቂቅ አዋጁ ንዑስ አንቀጽ 5(5) በአዲስ መልክ እንዲደነገግ ተደርጓል፡፡ 3.10 አሁን በሥራ ላይ ያለዉ አዋጅ አንቀፅ 6 አደዲስና ነባር ንዑስ አንቀፆችን በማካተት ተሻሽሏል፡፡ የአዋጁ ንዑስ አንቀጽ 6(1) ተሰርዞ የክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር ወይም የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪ ከብሔራዊ ባንክ ፈቃድ ወይም ይሁንታ ለማግኘት ማመልከቻ ማቅረብ እንዳለበት በሚጠይቅ አግባብ በአዲስ መልክ በረቂቅ አዋጁ ተመሳሳይ ንዑስ አንቀፅ እንዲደነገግ ተደርጓል፡፡ 3.11 ባንክ ወይም አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ ለማዉጣት የብሔራዊ ባንክን ይሁንታ ማግኘት እንዳለበት፣ ከፋይናንስ ተቋምና ከመንግሥት ድርጅት ዉጭ በክፍያ ስርዓት ዘርፍ ለመሰማራት የሚፈልግ ማንኛዉም የንግድ ማህበር ተቀጥላ ወይም ራሱን የቻለ ኩባንያ ማቋቋም እንደሚያስፈልግ፣ የመንግሥት ድርጅት በክፍያ ስርዓት ዘርፍ እንዲሰማራ በልዩ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ሊፈቀድ እንደሚገባዉ፣ የዉጭ አገር ዜጎች በክፍያ ሥርዓት ዘርፍ በዉጭ አገር ገንዘብ ሙአለ ንዋያቸዉን ሊያፈስሱ ወይም ተቀጥላ ሊያቋቁሙ እንደሚችሉ፣ ለስትራቴጂክ ድርጅቶች ማለትም ለቴሌኮም ኦፕሬተር፣ ለክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አዉጪና ለክፍያ ስርዓት ኦፕሬተር ተጨማሪ ዕድል ለመስጠትና...